ምሳሌ 8:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥ በፍርድ ጎዳና መካከልም እመላለሳለሁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፤ በፍትሕም ጐዳና እጓዛለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥ በፍርድም ጎዳና መካከል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኔ መንገድ የጽድቅ መንገድ ነው፤ እኔ የምከተለው የፍትሕን ፈለግ ነው። |
ለሚወድዱኝ ሀብትን እከፍላቸው ዘንድ ቤተ መዛግብታቸውንም በመልካም ነገር እሞላ ዘንድ። የሚሆነውን ነገር በየቀኑ ብነግራችሁ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን ቍጥር አስባለሁ።
ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፥ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን” ይላሉ።
የሚራራላቸውም ያጽናናቸዋልና፥ በውኃ ምንጮችም በኩል ይመራቸዋልና አይራቡም፤ አይጠሙም፤ የፀሐይ ትኩሳትም አይጐዳቸውም።
ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ቃሉን ይሰሙታል፤ እርሱም በጎቹን በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ አውጥቶም ያሰማራቸዋል።
በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”