ዋጋው ብዙ ከሆነ ዕንቍ ጥበብ ትበልጣለችና፥ የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም።
ጥበብ ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናትና፤ ከምትመኙት ነገር ሁሉ አንዳች የሚስተካከላት የለም።
ጥበብ ከዕንቁ ትበልጣለችና የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም።
“እኔ ጥበብ፥ ከዕንቊ የምበልጥ ስለ ሆንኩ ምንም ነገር ብትመኙ ከእኔ የሚወዳደር አንድም ነገር የለም።
ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ከወርቅ ይመረጣል። ዕውቀትንም ገንዘብ ማድረግ ከብር ይሻላል።
ወርቅና ብዙ ቀይ ዕንቍ ይገኛል፤ የዕውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።
ጥበብ ከርስት ጋር መልካም ነው፤ ፀሓይንም ለሚያዩ ሰዎች ትርፍን ይሰጣል።
ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?
ሰምተን እናደርጋት ዘንድ ስለ እኛ ባሕሩን ተሻግሮ እርስዋን የሚያመጣልን ማን ነው? እንዳትል ከባሕሩ ማዶ አይደለችም።