ምሳሌ 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዐይንህ እንቅልፍን፥ ለሽፋሽፍቶችህም ሸለብታን አትስጥ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐይኖችህ እንቅልፍ አይያዛቸው፣ ሽፋሽፍቶችህም አያንጐላጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዓይንህ እንቅልፍን ለሽፋሽፍቶችህም እንጉልቻን አትስጥ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንን ሳታደርግ አትተኛ፤ በዐይንህም እንቅልፍ አይዙር። |
ልጄ ሆይ፥ እኔ የማዝዝህን አድርግ፤ ራስህንም አድን፤ ስለ ወዳጅህ በክፉዎች እጅ ወድቀሃልና፤ ሰነፍ አትሁን፥ የተዋስኸውን ወዳጅህን አነሣሣው።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
የእግዚአብሔር መልአክ ወደ መጠመቂያዉ ወርዶ ውኃዉን በሚያናውጠው ጊዜ፥ ከውኃዉ መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ ወርዶ የሚጠመቅ ካለበት ደዌ ሁሉ ይፈወስ ነበርና።