እንግዲህ ድህነት እንደ ክፉ መልእክተኛ፥ ችግርም እንደ ደኅና ርዋጭ ይመጣብሃል። ሰነፍ ባትሆን ግን ባለጸግነትህ እንደምንጭ ይመጣልሃል፤ ችግርም እንደ ክፉ ርዋጭ ከአንተ ይርቃል።
ድኽነት እንደ ወንበዴ፣ ዕጦትም መሣሪያ እንደ ታጠቀ ሰው ከተፍ ይልብሃል።
እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥ ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።
ገና ተኝተህ ሳለ ድኽነትና ማጣት የጦር መሣሪያ እንደ ታጠቀ ወንበዴ በድንገት ይደርሱብሃል።
የሐኬተኛ እጅ ችግረኛ ያደርጋል፤ የትጉህ እጅ ግን ባለጠጋ ያደርጋል።
የማይሠራ ሁሉ በምኞት ይኖራል። የደጋጎች እጅ ግን ይተጋል።
ችግረኛን ሰው ሽብር ይይዘዋል፥ የማይሠራ ሰውም ይራባል።
እንዳትወገድ ማማትን አትውደድ። ድሃም እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ ዐይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ።
ታካች ሰው ሲያሽሟጥጡት አያፍርም፤ ስለዚህ በመከር ጊዜ ይለምናል፥ የሚሰጠውም የለም። በክምሩ እያለ ስንዴ የሚበደር እንደዚሁ ነው።
ሰካራምና አመንዝራ ይደኸያል፥ እንቅልፋምም ሁሉ የተቦጫጨቀ ጨርቅ ይለብሳል።
እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን በቃሉ አንዳች አትጨምር።
ሁለትን ነገር ከአንተ እለምናለሁ፥ ሳልሞትም የሰጠኸኝን ጸጋህን አትከልክለኝ፤
ሰነፍ እጆቹን ኰርትሞ ይቀመጣል፥ የገዛ ሥጋውንም ይበላል።