ጥቂት ትተኛለህ፥ ጥቂትም ትቀመጣለህ፥ ጥቂት ታሸልባለህ፥ ጥቂትም እጆችህን በደረትህ ታጥፋለህ፤
ጥቂት ማንቀላፋት፤ ጥቂት ማንጐላጀት፤ እጅን አጣጥፎ ጥቂት ጋደም ማለት፤
ጥቂት መተኛት፥ ጥቂት ማንቀላፋት፥ ለመተኛት ጥቂት እጅን ማጣጠፍ፥
“ጥቂት እተኛለሁ፤ ጥቂት አንቀላፋለሁ፤ እጄንም አጣጥፌ ለጥቂት ጊዜ ዐርፋለሁ” ስትል፥
ችግረኛን ሰው ሽብር ይይዘዋል፥ የማይሠራ ሰውም ይራባል።
እንዳትወገድ ማማትን አትውደድ። ድሃም እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ ዐይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ።
ሰካራምና አመንዝራ ይደኸያል፥ እንቅልፋምም ሁሉ የተቦጫጨቀ ጨርቅ ይለብሳል።
አንተ ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገዱንም ተመልክተህ ቅና። ከእርሱም ይልቅ ብልህ ሁን።
አንተ ታካች እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ?
ሰነፍ እጆቹን ኰርትሞ ይቀመጣል፥ የገዛ ሥጋውንም ይበላል።