ለአንተ ብቻ ይሁኑ፥ ከአንተ ጋር ላሉ እንግዶችም አይሁኑ።
ለአንተ ብቻ ይሁኑ፤ ባዕዳን አይጋሩህ።
ጒድጓድህና ምንጭህ ማንም ሰው ከአንተ ጋር የማይካፈላቸው የአንተ ብቻ ይሁኑ።
ከምንጮችህ ውኆች ወደ ሜዳ አይፍሰሱ። ውኃዎችም ወደ አደባባዮች አይሂዱ፥
የውኃ ምንጭህ ለአንተ ይሁንልህ፤ ከልጅነት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።