ምሳሌ 4:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠብቃት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አክብራት፥ እርስዋም ታቅፍሃለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክብርን ስጣት፤ ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ ዕቀፋት፤ ታከብርሃለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፍ ከፍ አድርጋት፥ እርሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፥ ብታቅፋትም ታከብርሃለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብን አክብራት፤ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አጥብቀህም ብትይዛት፥ ክብርን ትሰጥሃለች። |
ረጅም ዕድሜና የሕይወት ዘመን በቀኝዋ ነው። ባለጠግነትና ክብርም በግራዋ፥ ከአፏ ጽድቅ ይወጣል። ሕግንና ምጽዋትንም በአንደበትWa ትለብሳለች።
ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት፤ ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም።