ልጄ ሆይ፥ የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።
የወለደህን አባትህን አድምጥ፤ እናትህንም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።
የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።
የወለደህ እርሱ ስለ ሆነ የአባትህን ምክር ስማ፤ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።
ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ትእዛዝ ቸል አትበል፤
ብልህ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ አላዋቂ ልጅ ግን እናቱን ያሰድባል።
ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ሕጎች ጠብቅ፥ የእናትህንም ትእዛዝ ቸል አትበል፤
ከእናንተ እያንዳንዱ አባቱንና እናቱን ይፍራ፤ ሰንበታቴንም ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
“በሽበታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማግሌውንም አክብር፤ አምላክህን እግዚአብሔርንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
ሙሴ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤’ ደግሞም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት፤’ ብሎአልና።
“አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።