በከንፈሮችህ ቃሌ ብትኖር ለከንፈሮቼ የቀኑ ይሆናሉ።
ከንፈሮችህ ትክክሉን ቢናገሩ፣ ውስጣዊ ሁለንተናዬ ሐሤት ያደርጋል።
ከንፈሮችህም በቅን ቢናገሩ ኩላሊቶቼ ደስ ይላቸዋል።
ትክክለኛ ቃል በምትናገርበት ጊዜ ኲራት ይሰማኛል።
ልብህ በኀጢአተኞች አይቅና፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤
የተወደደች ነገርን እናገራለሁና ስሙ፤ ከከንፈሮቼም ቅን ነገርን አወጣለሁ፤
የሚሰሙአችሁ ሞገስን ያገኙ ዘንድ፥ ግዳጃችሁ እንዲፈጸም መልካም ነገር እንጂ ክፉ ነገር ሁሉ ከአፋችሁ አይውጣ።
የሚያሳፍር ነገርም፥ የስንፍና ነገርም፥ ወይም የማይገባ የዋዛ ነገር በእናንተ ዘንድ አይሁን፤ ማመስገን ይሁን እንጂ።
ልናገርም እንደሚገባኝ እገልጠው ዘንድ ጸልዩልኝ።
ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።