ሕፃናትን ከመቅጣት ቸል አትበል፥ በበትር ብትመታቸው አይሞቱምና።
ልጅን ከመቅጣት ወደ ኋላ አትበል፤ በአርጩሜ ብትገርፈው አይሞትም።
ልጅን ከመቅጣት ቸል አትበል፥ በበትር ብትመታው አይሞትምና።
ልጅን በሥነ ሥርዓት ከመቅጣት አትቦዝን፤ በአርጩሜ ብትመታው አይሞትም፤
በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፤ ልጁን የሚወድድ ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል።
ለተስፋ ይሆንህ ዘንድ ልጅህን ግረፍ፥ ለመሳደብ ግን እጅህን አታንሣ፥
አለማወቅ የጐልማሳን ልብ ከፍ ከፍ አደረገች፤ በትርና ተግሣጽ ከእርሱ ርቀዋልና።
ልብህን ለተግሣጽ ስጥ፥ ጆሮህንም ለዕውቀት ቃል አዘጋጅ።
ቅጣታችሁን ታገሡ፤ ልጆቹ እንደ መሆናችሁ ይወዳችኋልና፤ አባቱ የማይቈጣው ልጅ ማን ነው?