ምሳሌ 23:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመኳንንት ማዕድ ለመብላት በተቀመጥህ ጊዜ፥ ያቀረቡልህን ፈጽመህ ዕወቅ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከገዥ ጋራ ለመብላት በምትቀመጥበት ጊዜ፣ በፊትህ ያለውን በሚገባ አስተውል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከባለ ሥልጣን ጋር ለመብላት በተቀመጥህ ጊዜ፥ በፊትህ ያለውን በደኅና አስተውል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከባለ ሥልጣን ጋር ለመመገብ በአንድ ገበታ ላይ ብትቀርብ ማንነቱን አትዘንጋ፤ |
እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥