ታካች ሰው በላኩት ጊዜ ያመካኛል፥ እንዲህም ይላል፦ “አንበሳ በመንገድ አለ፥ በአደባባይም ግድያ አለ።”
ሰነፍ፣ “አንበሳ በውጭ አለ፤ በጐዳና ላይ እገደላለሁ” ይላል።
ሰነፍ ሰው፦ “ውጪ አንበሳ አለ፤ ብወጣ፥ በመንገዱ ላይ እሞታለሁ” ይላል።
ሰነፍ ሰው “ውጪ አንበሳ አለ፤ ብወጣ ይገድለኛል” ብሎ ይከራከራል። “አንበሳ ያገኘኛል” በማለት ከቤቱ አይወጣም።
የሰነፎች መንገዶች እሾህ የተከሰከሰባቸው ናቸው፥ የጽኑዓን መንገዶች ግን ጥርጊያ ናቸው።
ችግረኛን ሰው ሽብር ይይዘዋል፥ የማይሠራ ሰውም ይራባል።
የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ ኃጥእ ግን የጥበብን ቃል ይንቃል።
ቀሚሴን አወለቅሁ፥ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ፥ እንዴት አሳድፈዋለሁ?