ምሳሌ 20:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሽብርና ስደት ክፉዎችን ድንገት ይገናኛቸዋል፥ ግርፋትም ወደ ሆድ ዕቃ ይገባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያቈስል በትር ክፋትን ያስወግዳል፤ ግርፋትም የውስጥ ሰውነትን ያጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰንበር ቁስል ክፉዎችን ያነጻል፥ ግርፋትም ወደ ሆድ ጉርጆች ይገባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያቈስል ቅጣት ክፉ ነገርን ያስወግዳል፤ ግርፋትም የሰውን ውስጣዊ ሁኔታ ያነጻል። |
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፤ ይህም ኀጢአትን የማስወገድ ፍሬ ሁሉ ነው።
እርሱ ግን ስለ ኀጢአታችን ቈሰለ፤ ስለ በደላችንም ታመመ፤ የሰላማችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡናል፤ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።