እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
ምሳሌ 20:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው መንፈስ የሆድን መዛግብት የሚመረምር፥ የእግዚአብሔር መብራት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው መንፈስ ለእግዚአብሔር መብራት ነው፤ ውስጣዊ ማንነቱንም ይፈትሻል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው መንፈስ የጌታ መብራት ነው የሆዱን ጉርጆች ሁሉ የሚመረምር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ስለ ሆነ የሰውን ውስጣዊ ሰውነት ሁሉ ይመረምራል። |
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ፤ ከሥራቸውም የተነሣ ይታወቃል፤ ሕሊናቸውም ይመሰክርባቸዋል፤ ይፈርድባቸዋልም።
በሰው ልቡና ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? በእርሱ ያለችው ነፍሱ ናት እንጂ፤ እንዲሁም ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር የእግዚአብሔርን አሳብ የሚያውቅ የለም።