በውስጥዋም የነበሩትን ሕዝብ አውጥቶ በመጋዝና በብረት መቈፈሪያ በብረት መጥረቢያም ሥር አኖራቸው፤ በሸክላ ጡብ እቶንም አሳለፋቸው። በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። ዳዊትም፥ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
ምሳሌ 20:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብልህ ንጉሥ የኃጥኣን መንሽ ነው፥ በእነርሱ ላይም መንኰራኵርን ይነዳባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቢብ ንጉሥ ክፉዎችን አበጥሮ ይለያል፤ የመውቂያ መንኰራኵርንም በላያቸው ላይ ይነዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠቢብ ንጉሥ ኀጥኣንን በመንሽ ይበትናቸዋል፥ መንኰራኵሩንም በእነርሱ ላይ ያንኰራኩርባቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብልኅ ንጉሥ ዐመፀኞችን ለይቶ ያውቃቸዋል፤ ያለ ምሕረትም ይቀጣቸዋል። |
በውስጥዋም የነበሩትን ሕዝብ አውጥቶ በመጋዝና በብረት መቈፈሪያ በብረት መጥረቢያም ሥር አኖራቸው፤ በሸክላ ጡብ እቶንም አሳለፋቸው። በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። ዳዊትም፥ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።