ምሳሌ 20:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሐሰት እንጀራ ለሰው የጣፈጠ ነው፤ ከዚህ በኋላ ግን አፉ ጭንጫ ይሞላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ይጣፍጠዋል፤ በመጨረሻ ግን አፉን ኰረት ሞልቶት ያገኘዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐሰት እንጀራ ለሰው የጣፈጠ ነው፥ ከዚያ በኋላ ግን አፉ ጭንጫ ይሞላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማጭበርበር የምታገኘው ነገር እንደ ጣፋጭ ምግብ ሊያስደስትህ ይችላል፤ ነገር ግን ውሎ ሲያድር በአፍ ውስጥ እንደ አሸዋ ይሆናል። |
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።