ምሳሌ 20:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚገዛ ሰው፦ “ክፉ ነው፥ ክፉ ነው” ይላል፤ በሄደ ጊዜ ግን ይመካል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕቃ የሚገዛ፣ “የማይረባ ነው፤ የማይረባ ነው” ብሎ ያራክሳል፤ ሲመለስ ግን በግዥው ይኵራራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕቃ የሚገዛ “አይረባም አይረባም” ብሎ ያራክሳል፥ ገዝቶ ሲመለስ ግን በገዛው ዕቃ ይኩራራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገዢ ዘወትር መጥፎ ነው እያለ ዕቃን ያራክሳል፤ ገዝቶ ከሄደ በኋላ ግን “በርካሽ ገዛሁ” እያለ ይመካል። |
ጊዜው መጥቶአል፤ ቀኑ እነሆ ቀርቦአል፤ መቅሠፍቷ በሁለንተናዋ መልቶአልና የሚገዛ ደስ አይበለው፤ የሚሸጥም አይዘን።
አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።