የጽድቅን ጎዳና ይጠብቃል፤ የሚፈሩትንም መንገድ ያጸናል።
የፍትሕን መንገድ ይጠብቃል፤ የታማኞቹንም አካሄድ ያጸናል።
የፍርድን ጎዳና ይጠብቃል፥ የቅዱሳኑንም መንገድ ያጸናል።
የፍትሕን ሂደት ይከታተላል፤ በታማኝነት የሚያገለግሉትንም ይጠብቃል።
እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የኃጥኣን መንገድ ግን ትጠፋለች።
ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?
እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥ በፍርድ ጎዳና መካከልም እመላለሳለሁ፥
አንበሳ አይኖርበትም፤ ክፉ አውሬም አይወጣበትም፤ በዚያም አይገኙም፤ የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ።
ለሕዝቡም ራራላቸው፤ ቅዱሳን ሁሉ ከእጅህ በታች ናቸው፤ እነርሱም የአንተ ናቸው። ቃሎችህንም ይቀበላሉ።
ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው፤
ለሚጸልይ ጸሎቱን ይሰጠዋል፤ የጻድቃንን ዘመን ይባርካል፤ የሰው ኀይል ጽኑዕ አይደለምና።