ምሳሌ 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጆሮህ ጥበብን ትሰማለች፥ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ። ልብህንም ልጅህን ለመምከር ታቀርባለህ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣ ልብህንም ወደ ማስተዋል ብትመልስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጆሮህ ጥበብን እንዲያደምጥ ታደርጋለህ፥ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጥበብን ቃል አድምጥ፤ በጥንቃቄም አስተውለው። |
አውቅና እመረምር ዘንድ ጥበብንና የነገሩን ሁሉ መደምደሚያ እፈልግ ዘንድ፥ የክፉዎችንም ስንፍናና ዕብደት አውቅ ዘንድ እኔ በልቤ ዞርሁ።
ጥበብን አውቅ ዘንድ በምድር የሚሆነውንም ድካም አይ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ በቀንና በሌሊት እንቅልፍን በዐይኑ የሚያይ የለምና።
ይህን ሁሉ በአንድነት አየሁ፥ ከፀሓይም በታች ወደ ተደረገው ሥራ ሁሉ ልቤን ሰጠሁ፤ ሰውም ሰውን ለመጕዳት ገዥ የሚሆንበት ጊዜ አለ።
ስሙኝ፤ ጎዳናዬን ተከተሉ፤ አድምጡኝም፤ ሰውነታችሁም በበረከት ትኖራለች፤ የታመነችዪቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
በተሰሎንቄ ካሉትም እነርሱ ይሻላሉ፤ በፍጹም ደስታ ቃላቸውን ተቀብለዋልና፤ ነገሩም እንደ አስተማሩአቸው እንደ ሆነ ለመረዳት ዘወትር መጻሕፍትን ይመረምሩ ነበር።