ምሳሌ 19:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በከንፈሩ ከሚወሳልት አላዋቂ ይልቅ፥ ያለ ነውር የሚሄድ ድሃ ይሻላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንግግሩ ጠማማ ከሆነ ሞኝ ሰው ይልቅ፣ ያለ ነውር የሚሄድ ድኻ ሰው ይሻላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከንፈሩ ከሚወሳልት ሰነፍ ይልቅ ያለ ነውር የሚሄድ ድሀ ይሻላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንግግሩ ከሚቀላምድ ሞኝ ሰው ይልቅ በቅንነት የሚኖር ድኻ ሰው ይሻላል። |
ራሱን የሚያውቅ ሰው ለራሱ ጻድቅ ነው፤ የክፉዎች ሥራ ግን መልካም አይደለም። የሚበድሉ ሰዎችን ክፉ ይከተላቸዋል፥ የኃጥኣን መንገዳቸውም ታስታቸዋለች።
እጃችሁ በደም ጣታችሁም በኀጢአት ተሞልትዋል፤ ከንፈራችሁም ዐመፅን ተናግሮአል፤ ምላሳችሁም ኀጢአትን አሰምቶአል።
ስለዚህም በጌታችንና በቤቱ ሁላ ክፉ ነገር እንዲመጣ ተቈርጦአልና፥ እርሱ ክፉ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊናገረው አይችልምና የምታደርጊውን ተመልከቺና ዕወቂ።”
በዚህ ክፉ ሰው በናባል ላይ ጌታዬ ልቡን እንዳይጥል እለምናለሁ፤ እንደ ስሙ እንዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስንፍናም አድሮበታል፤ እኔ ባሪያህ ግን አንተ የላክሃቸውን ብላቴኖችህን አላየሁም።