ምሳሌ 16:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠቢብ ልብ ከአፉ ይታወቃል፥ በከንፈሩም ዕውቀትን ይለብሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠቢብ ሰው ልብ አንደበቱን ይመራል፤ ከንፈሮቹም ዕውቀትን ያዳብራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠቢብ ልብ አፉን ያስተምራል፥ ለከንፈሩም ትምህርትን ይጨምራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጥበበኛ ሰው አእምሮ ንግግሩን ይቈጣጠራል፤ ከአፉም የሚወጣው ንግግር ትምህርትን ያስፋፋል። |
የጻድቃን ልብ ታማኝነትን ይማራል፤ የኃአጥኣን አፍ ግን ክፋትን ይመልሳል። የደጋግ ሰዎች መንገዶች በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደዱ ናቸው፥ ስለ እነርሱም ጠላቶች ወዳጆችን ይሆናሉ።
በጥበብ ሁሉ እንድትበለጽጉ የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ዘንድ ይጽና፤ በመንፈስም ራሳችሁን አስተምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝሙርንና ምስጋናን፥ የቅድስና ማሕሌትንም በልባችሁ በጸጋ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።