ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ከወርቅ ይመረጣል። ዕውቀትንም ገንዘብ ማድረግ ከብር ይሻላል።
ከወርቅ ይልቅ ጥበብን ማግኘት፣ ከብርም ማስተዋልን መምረጥ ምንኛ ይበልጣል!
ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።
ወርቅን ከማግኘት ጥበብን ማግኘት ይበልጣል፤ ብርንም ከማግኘት ዕውቀትን ማግኘት ይሻላል።
እርስዋንም እንደ ብር ብትፈልጋት፥ እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት፤
ጥበብን የሚያገኝ፥ ማስተዋልንም የሚያውቅ መዋቲ ሰው ብፁዕ ነው።
በወርቅና በብር፥ በብዙም መዛግብት ከመነገድ ይልቅ በእርስዋ መነገድ ይሻላልና።
የአፌንም ቃል ቸል አትበል።
ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።
ከወርቅና ከከበረ ዕንቍ ይልቅ እኔን መምረጥ ይሻላል፥ ፍሬዬም ከጠራ ብር ይሻላል።
የጥበብ ጥላ ከብር ጥላ ይሻላል፤ የጥበብንም ዕውቀት ማብዛት ገንዘብ ላደረጋት ሕይወትን ትሰጠዋለች።
ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?
ሀብትን ለራሱ የሚሰበስብ፤ ሀብቱም ከእግዚአብሔር ያልሆነ እንዲሁ ነው።”