በፀሐይ ውስጥ ድንኳኑን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ በመንገዱ እንደሚራመድ አርበኛ ደስ ይለዋል።
ምሳሌ 14:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ትእዛዝ የሕይወት ምንጭ ነው። ሰዎችንም ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጡ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤ ሰውን ከሞት ወጥመድ ያድነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ ጌታን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤ ስለዚህ ከሞት ወጥመድ ለማምለጥ ከፈለግህ እግዚአብሔርን ፍራ። |
በፀሐይ ውስጥ ድንኳኑን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ በመንገዱ እንደሚራመድ አርበኛ ደስ ይለዋል።
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረች ነገርን አገኘሁ፤ እርስዋም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ በእጆችዋም ማሰሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ደግ የሆነ ከእርሷ ያመልጣል። ኀጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
በድኅነታችን መዝገብ በሕግ ይሰበስቡአቸዋል፤ ጥበብና ምክር፥ ጽድቅም ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው፤ እነዚህም የጽድቅ መዝገቦች ናቸው።