ጥበብ የጐደለው የሀገሩን ሰው ይንቃል። ብልህ ሰው ግን ጸጥታን ያመጣል።
ልበ ቢስ ባልንጀራውን ያንኳስሳል፤ አስተዋይ ግን አንደበቱን ይገዛል።
ወዳጁን የሚንቅ ልበ ጐደሎ ነው፥ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል።
በንቀት ተናግሮ ሰውን የሚያዋርድ፥ ማስተዋል የጐደለው ነው፤ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል።
ሕዝቡም ዝም አሉ፥ አንዳችም ቃል አልመለሱለትም፤ ንጉሡ እንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና።
ኃጥእ ከነገር ብዛት የተነሣ ከኀጢአት አያመልጥም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።
በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤ በኃጥኣን አፍ ግን ትገለበጣለች።
ሁለት ምላስ የሆነ ሰው የጉባኤን ምሥጢር ይገልጣል፤ በአንደበቱ የታመነ ግን ነገርን ይሰውራል።
ድሃውን የሚንቅ ኀጢአትን ይሠራል፤ ለድሃ የሚራራ ግን ብፁዕ ነው።
አመንዝራ ግን በአእምሮው ጉድለት፥ ነፍሱ የሚጠፋበትን ጥፋት ይሠራል።
ገንዘብን የሚወዱ ፈሪሳውያንም ይህን ሁሉ ነገር ሰምተው ተጠቃቀሱበት።
ራሳቸውን ለሚያመጻድቁና ባልንጀራቸውን ለሚንቁ እንዲህ ብሎ መሰለላቸው።
ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
ዜቡልም፥ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ያልህበት አፍህ አሁን የት አለ? ይህ የናቅኸው ሕዝብ አይደለምን? አሁንም ወጥተህ ከእነርሱ ጋር ተዋጋ” አለው።
ክፉዎች ሰዎች ግን፥ “ያድነን ዘንድ ይህ ሰው ማን ነው?” ብለው ናቁት፤ እጅ መንሻም አላመጡለትም።