የጻድቃን ከንፈሮች ሞገስን ያፈስሳሉ፤ የኃጥኣን አፍ ግን ከዕውቀት ይከለከላል።
የጻድቃን ከንፈሮች ተገቢውን ነገር ያውቃሉ፤ የክፉዎች አንደበት ግን የሚያውቀው ጠማማውን ብቻ ነው።
የጻድቅ ከንፈሮች ደስ የሚያሰኝ ነገርን ያውቃሉ፥ የክፉዎች አፍ ግን ጠማማ ነገር ይናገራል።
የደጋግ ሰዎች ንግግር ተስማሚ ነው፤ የክፉዎች ንግግር ግን ጠማማ ነው።
በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤ በኃጥኣን አፍ ግን ትገለበጣለች።
በሐሰት የሚመሰክሩ በሰይፍ ይገድላሉ፤ በአፋቸው ሰይፍ አለና። የጠቢባን ምላስ ግን የቈሰለውን ይፈውሳል።
የኃጥኣን ምክር ተንኮል ነው። የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል።
የጠቢባን ምላስ መልካም ነገርን ታውቃለች፤ የአላዋቂዎች አፍ ግን ክፋትን ይናገራል።
የጻድቃን ልብ ታማኝነትን ይማራል፤ የኃአጥኣን አፍ ግን ክፋትን ይመልሳል። የደጋግ ሰዎች መንገዶች በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደዱ ናቸው፥ ስለ እነርሱም ጠላቶች ወዳጆችን ይሆናሉ።
አንተን ከክፉ መንገድ፥ ምንም የሚታመን ነገርን ከማይናገር ሰውም ታድንህ ዘንድ፥
ክፉ አፍን ከአንተ አርቅ፥ ሐሰተኞች ከንፈሮችንም ከአንተ አስወግድ።
ዓመፀኛና ሰነፍ የሆነ ሰው ቀና ያልሆኑ መንገዶችን ይሄዳል፤
የጠቢብ ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት፤ የሰነፍ ከንፈሮች ግን ራሱን ይውጡታል።
ሰባኪውም ያማረውን በቅንም የተጻፈውን እውነተኛውንም ቃል መርምሮ ለማግኘት ፈለገ።