ምሳሌ 1:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብ በጎዳና ትመሰገናለች፤ በአደባባይም ድምፅዋን ትሰጣለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበብ በጐዳና ላይ ጮኻ ትጣራለች፤ በየአደባባዩ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥበብ በጎዳና ትጮኻለች፥ በአደባባይ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብ በመንገድ ላይ ትጮኻለች፤ በአደባባይም ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ታሰማለች። |
ስለዚህ የእግዚአብሔር ጥበቡ እንዲህ አለች፦ እነሆ፥ እኔ ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ይገድላሉ፤ ያሳድዳሉም።
በኋለኛዪቱ በታላቅዋ የበዓል ቀንም ጌታችን ኢየሱስ ቆመና ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፥ “የተጠማ ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።
ለእኛ ለዳንነው ግን ከአይሁድ፥ ከአረሚም ብንሆን ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ የእግዚአብሔርም ጥበብ ነው።
እናንተም በኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱ ናችሁ፤ በእርሱም ከእግዚአብሔር ጥበብንና ጽድቅን፥ ቅድስናንና ቤዛነትን አገኘን።