መግደልን የለመዱ እነርሱ ክፋትን ለራሳቸው ይሰበስባሉ። የኀጢአተኞች ሰዎች አወዳደቃቸው ክፉ ነው።
እነዚህ ሰዎች የሚያደቡት በገዛ ደማቸው ላይ ነው፤ የሚሸምቁትም በራሳቸው ላይ ብቻ ነው።
እነርሱም በደማቸው ላይ ያደባሉ፥ በነፍሳቸውም ላይ ይሸምቃሉ።
ይህን የሚያደርጉ ሰዎች የሚሞቱበትን ወጥመድ ራሳቸው ይዘረጋሉ።
እግዚአብሔር ፍርድን ማድረግ ያውቃል፤ ኀጢአተኛው በእጆቹ ሥራ ተጠመደ።
“ና ከእኛ ጋር ደምን በማፍሰስ አንድ ሁን፥ ጻድቅ ሰውንም በምድር እንቅበር፥ ብለው ቢማልዱህ፥
ወጥመድን ለወፎች በከንቱ የሚያጠምዱ አይደለምና፥
ጻድቅ ልጅ ለሕይወት ይወለዳል፤ የኃጥኣን መወለድ ግን ለሞት ነው።
የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፤ ኀጢአት ግን በክፉዎች ላይ ትወርዳለች።
ነገር ግን ልቡናህን እንደ ማጽናትህ፥ ንስሓም እንደ አለመግባትህ መጠን የእግዚአብሔር እውነተና ፍርድ በሚገለጥበት ቀን መቅሠፍትን ለራስህ ታከማቻለህ።