ኑ፥ እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፤ ክፉ አውሬም በላው እንላለን፤ ሕልሞቹም ምን እንደሚሆኑ እናያለን።”
ምሳሌ 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግራቸው ወደ ኀጢአት ይቸኵላል፤ ደም ለማፍሰስም ፈጣኖች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ክፉ ነገርን ለማድረግ ይሮጣሉ፤ ሰውን ለመግደልም ፈጣኖች ናቸው። |
ኑ፥ እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፤ ክፉ አውሬም በላው እንላለን፤ ሕልሞቹም ምን እንደሚሆኑ እናያለን።”
እግሮቻቸውም ለተንኮል ይሮጣሉ፤ ደምን ለማፍሰስም ይፈጥናሉ፤ ሰውን ለመግደል ይመክራሉ፤ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ።
በእኔ ኀጢአት የእግዚአብሔር ጽድቅ ከጸና እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር በሰው ላይ ቅጣትን ቢያመጣ ይበድላልን? አይበድልም፤ የምናገረውንም በሰው ልማድ እናገራለሁ።
ሳኦልም ዳዊትን ከግንብ ጋር ያጣብቀው ዘንድ ጦሩን ወረወረ፤ ዳዊትም ከሳኦል ፊት ዘወር አለ፤ ጦሩም በግንቡ ውስጥ ተተከለ፤ በዚያም ሌሊት ዳዊት ሸሸቶ አመለጠ።