ፊልጵስዩስ 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ እንዴት እንደ አለሁ በዐወቅሁ ጊዜ፥ እርሱን በቶሎ እንደምልከው ተስፋ አደርጋለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ የራሴን የወደ ፊት ሁኔታ እንዳጣራሁ ልልከው ተስፋ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ በእኔ ዘንድ ያለውን ሁኔታ አይቼ፥ እርሱን ቶሎ እንደምልክ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የእኔ ጉዳይ ከምን እንደሚደርስ ከተረዳሁ በኋላ ጢሞቴዎስን በፍጥነት ወደ እናንተ እንደምልክላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ እንዴት እንደምሆን ባየሁ ጊዜ፥ እርሱን ቶሎ እንድልክ ተስፋ አደርጋለሁ፤ |
ጢሞቴዎስን እንድልክላችሁ፥ እኔም ዜናችሁን ሰምቼ ደስ እንዲለኝ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋ አደርጋለሁ።
ዳዊትም ከዚያ በሞዓብ ምድር ወዳለችው ወደ መሴፋ ሄደ፤ የሞዓብንም ንጉሥ፥ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ አባቴና እናቴ ከአንተ ጋር ይቀመጡ ዘንድ እለምንሃለሁ” አለው።