ካህናቱና ሌዋውያኑም ተነሥተው ሕዝቡን ባረኩ፤ ድምፃቸውም ተሰማ፥ ጸሎታቸውም ወደ ቅዱስ ማደሪያው ወደ ሰማይ ዐረገ።
ዘኍል 8:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በኋላ ሌዋውያን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በአሮንና በልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ገቡ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረጉላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ሌዋውያኑ በአሮንና በልጆቹ ኀላፊነት ሥር ሆነው ድንኳን ውስጥ የሚፈጸመውን አገልግሎት ለማከናወን ገቡ። እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አስፈላጊውን በሌዋውያኑ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በአሮንና በልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ገቡ፤ ጌታ ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረጉላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለሙሴ ስለ ሌዋውያን በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሕዝቡ ሁሉን ነገር አደረጉ፤ በዚህም ዐይነት ሌዋውያን በአሮንና በልጆቹ ኀላፊነት ሥር በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል ዝግጁዎች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በአሮንና በልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ይሠሩ ዘንድ ገቡ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረጉላቸው። |
ካህናቱና ሌዋውያኑም ተነሥተው ሕዝቡን ባረኩ፤ ድምፃቸውም ተሰማ፥ ጸሎታቸውም ወደ ቅዱስ ማደሪያው ወደ ሰማይ ዐረገ።
ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው፥ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርቡና ያገለግሉ ዘንድ፥ ያመሰግኑም፥ ያከብሩም ዘንድ ካህናቱንና ሌዋውያኑን መደበ።
ነገር ግን በምስክሩ ድንኳንና በዕቃዎችዋ ሁሉ፥ በውስጥዋም ባለው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን አቁማቸው። ድንኳንዋንና ዕቃዎችዋን ሁሉ ይሸከሙ፤ ያገልግሉአትም፤ በድንኳንዋም ዙሪያ ይስፈሩ።
“ከዚያም በኋላ ሌዋውያን የምስክሩን ድንኳን አገልግሎት ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ፤ ታነጻቸውማለህ፤ ስጦታም አድርገህ በፊቴ ታቀርባቸዋለህ።
ሌዋውያንም ከኀጢአት ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ስጦታ አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት አቀረባቸው፤ አሮንም ያነጻቸው ዘንድ አስተሰረየላቸው።