ዘኍል 8:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋውያንንም ስጦታ አድርጌ አገባኋቸው፤ ልዩ በሆነች ድንኳን ውስጥ የእስራኤልን ልጆች ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ የእስራኤልንም ልጆች ኀጢአት ያቃልሉ ዘንድ ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ተሰጡ፤ ከእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደስ የሚቀርብ አይኑር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንን ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚፈጸመውን አገልግሎት እንዲያከናውኑና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ ቢቀርቡ እንዳይቀሠፉ ያስተሰርዩላቸው ዘንድ፣ ከእስራኤላውያን ሁሉ መካከል ሌዋውያኑን ስጦታ አድርጌ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻቸዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደሱ በቀረቡ ጊዜ መቅሠፍት እንዳያገኛቸው፥ ለእስራኤል ልጆች እንዲያስተስርዩላቸው፥ የእስራኤልንም ልጆች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲሠሩ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአቸዋለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤልን ሕዝብ ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲያገለግሉና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ በመቅረብ እንዳይቀሠፉ ይጠብቁአቸው ዘንድ፥ ሌዋውያንን ከእስራኤላውያን እንደ ስጦታ ተቀብዬ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደሱ በቀረቡ ጊዜ መቅሠፍት እንዳያገኛቸው፥ ለእስራኤል ልጆች ያስተሰርዩላቸው ዘንድ፥ የእስራኤልንም ልጆች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአቸዋለሁ። |
ነገር ግን በምስክሩ ድንኳንና በዕቃዎችዋ ሁሉ፥ በውስጥዋም ባለው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን አቁማቸው። ድንኳንዋንና ዕቃዎችዋን ሁሉ ይሸከሙ፤ ያገልግሉአትም፤ በድንኳንዋም ዙሪያ ይስፈሩ።
ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ላይ ዕዳ እንዳይሆንባቸው ሌዋውያን በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስፈሩ፤ ሌዋውያን የምስክሩን ድንኳን ሕግ ይጠብቁ።”
ሙሴም አሮንን፥ “ጥናህን ውሰድ፤ ከመሠዊያውም ላይ እሳት አድርግበት፤ ዕጣንም ጨምርበት፤ ወደ ማኅበሩም ፈጥነህ ውሰደው፤ አስተስርይላቸውም፤ ከእግዚአብሔር ፊት ቍጣ ወጥቶአልና፥ ሕዝቡንም ያጠፋቸው ዘንድ ጀምሮአል” አለው።
ሙሴና አሮን የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲሁ በሌዋውያን ላይ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉላቸው።
የኢያኮንዩ ልጆችም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተመልክተው ከቤትሳሚስ ሰዎች ጋር አልተቀበሉአትም፤ እግዚአብሔርም ከሕዝቡ አምስት ሺህ ሰባ ሰዎችን መታ፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ ግዳይ ስለ መታ ሕዝቡ አለቀሱ።