ከደኅንነቱም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፤ ስቡን፥ እስከ ጀርባውም ድረስ የተቈረጠ ሙሉ ላቱን፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥
ዘኍል 7:88 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የደኅንነትም መሥዋዕት ከብት ሁሉ፥ ሃያ አራት ጊደሮች፥ ስድሳም አውራ በጎች፥ ስድሳም አውራ ፍየሎች፥ ስድሳም ነውር የሌለባቸው የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመቀደሻው የቀረበ ቍርባን ይህ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኅብረት መሥዋዕት የቀረቡት እንስሳት ድምር ሃያ አራት በሬ፣ ስድሳ አውራ በግ፣ ስድሳ ተባዕት ፍየልና ስድሳ አንድ ዓመት የሆናቸው ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበር። እንግዲህ መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመሠዊያው መቀደስ የቀረቡ ስጦታዎች እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአንድነትም መሥዋዕት ከብት ሁሉ ሀያ አራት በሬዎች፥ ስልሳም አውራ በጎች፥ ስልሳም አውራ ፍየሎች፥ ስልሳም የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ በኋላ መሠዊያውን ለመቀደስ የቀረበ መባ ይህ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአንድነት መሥዋዕት የቀረቡት የከብት ብዛት፦ ኻያ አራት ኰርማዎች፥ ሥልሳ አውራ በጎች፥ ሥልሳ ተባት ፍየሎች፥ ባለ አንድ ዓመት ዕድሜ ሥልሳ ተባት በጎች፥ መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመቅደስ የቀረበ ቊርባን ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የደኅንነትም መሥዋዕት ከብት ሁሉ ሀያ አራት በሬዎች፥ ስድሳም አውራ በጎች፥ ስድሳም አውራ ፍየሎች፥ ስድሳም የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመቀደሻው የቀረበ ቍርባን ይህ ነበረ። |
ከደኅንነቱም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፤ ስቡን፥ እስከ ጀርባውም ድረስ የተቈረጠ ሙሉ ላቱን፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ድንኳኑን ፈጽሞ በተከለባት፥ እርስዋንና ዕቃዋን ሁሉ በቀባና በቀደሰባት፥ መሠዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ በቀባና በቀደሰባት ቀን፥
መሠዊያውም በተቀባ ቀን አለቆቹ መሠዊያውን ለመቀደስ ቍርባንን አቀረቡ፤ አለቆችም መባቸውን በመሠዊያው ፊት አቀረቡ።
መሠዊያው በተቀባ ቀን የእስራኤል ልጆች አለቆች ለመሠዊያው መቀደሻ ያቀረቡት መባ ይህ ነበረ፤ ዐሥራ ሁለት የብር ወጭቶች፥ ዐሥራ ሁለት የብር ድስቶች፥ ዐሥራ ሁለት የወርቅ ጭልፋዎች፤
የሚቃጠለው መሥዋዕት ከብት ሁሉ ከእህሉ ቍርባን ጋር ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ ዐሥራ ሁለትም አውራ በጎች፥ ዐሥራ ሁለትም የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበሩ፤ የኀጢአትም መሥዋዕት አውራ ፍየሎች ዐሥራ ሁለት ነበሩ።