ለማፍሰሻም ይሆኑ ዘንድ ወጭቶችዋን፥ ጭልፋዎችዋንም፥ መቅጃዎችዋንም፥ ጽዋዎችዋንም አድርግ፤ እነርሱንም ከጥሩ ወርቅ አድርጋቸው።
ዘኍል 7:84 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሠዊያው በተቀባ ቀን የእስራኤል ልጆች አለቆች ለመሠዊያው መቀደሻ ያቀረቡት መባ ይህ ነበረ፤ ዐሥራ ሁለት የብር ወጭቶች፥ ዐሥራ ሁለት የብር ድስቶች፥ ዐሥራ ሁለት የወርቅ ጭልፋዎች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሠዊያው በተቀባ ቀን የእስራኤል አለቆች የመሠዊያውን መቀደስ ምክንያት በማድረግ ያቀረቧቸው ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፤ ዐሥራ ሁለት የብር ሳሕኖች፣ ዐሥራ ሁለት ከብር የተሠሩ ጐድጓዳ ሳሕኖችና ዐሥራ ሁለት የወርቅ ጭልፋዎች፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሠዊያው በተቀባ ቀን የእስራኤል አለቆች መሠዊያውን ለመቀደስ ያቀረቡት መባ ይህ ነበረ፤ ዐሥራ ሁለት የብር ወጭቶች፥ ዐሥራ ሁለት የብር ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ ዐሥራ ሁለት የወርቅ ሙዳዮች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሠዊያው በተቀባ ቀን መሠዊያው እንዲቀደስበት ያቀረቡት መባ ይህ ነበር፦ ዐሥራ ሁለት ከብር የተሠሩ ዝርግ ሳሕኖች፥ ዐሥራ ሁለት ከብር የተሠሩ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ ዐሥራ ሁለት ከወርቅ የተሠሩ የዕጣን ማስቀመጫዎች፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሠዊያው በተቀባ ቀን የእስራኤል አለቆች ለመቀደሻው ያቀረቡት ቍርባን ይህ ነበረ፤ አሥራ ሁለት የብር ወጭቶች፥ አሥራ ሁለት የብር ድስቶች፥ አሥራ ሁለት የወርቅ ጭልፋዎች፤ |
ለማፍሰሻም ይሆኑ ዘንድ ወጭቶችዋን፥ ጭልፋዎችዋንም፥ መቅጃዎችዋንም፥ ጽዋዎችዋንም አድርግ፤ እነርሱንም ከጥሩ ወርቅ አድርጋቸው።
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ድንኳኑን ፈጽሞ በተከለባት፥ እርስዋንና ዕቃዋን ሁሉ በቀባና በቀደሰባት፥ መሠዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ በቀባና በቀደሰባት ቀን፥
መሠዊያውም በተቀባ ቀን አለቆቹ መሠዊያውን ለመቀደስ ቍርባንን አቀረቡ፤ አለቆችም መባቸውን በመሠዊያው ፊት አቀረቡ።
ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት ጊደሮች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ የዔናን ልጅ የአኪሬ መባ ይህ ነበረ።
እያንዳንዱም የብር ወጭት መቶ ሠላሳ ሰቅል፥ እያንዳንዱም ድስት ሰባ ሰቅል ነበረ፤ የዚህም ዕቃ ሁሉ ብር በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ነበረ።