ዘኍል 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ ራሱን አይላጭ፤ ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ ቅዱስ ይሆናል፤ የራሱንም ጠጕር ያሳድጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ስእለት ተስሎ ራሱን በለየበት ጊዜ ሁሉ ምላጭ ራሱን አይንካው፤ ለእግዚአብሔር የተለየበት ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ የተቀደሰ ይሁን፤ የራስ ጠጕሩንም ያሳድግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ለጌታ የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰ ይሆናል፥ የራሱንም ጠጉር ያሳድግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስእለት ተስሎ በናዝራዊነት እስካለ ድረስ ራሱን ምላጭ አይንካው፤ የናዝራዊነት ጊዜው እስኪፈጸም ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ (የተቀደሰ) ይሆናል፤ የራሱንም ጠጒር ያሳድጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ በራሱ ላይ ምላጭ አይደርስም፤ ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰ ይሆናል፥ የራሱንም ጠጕር ያሳድጋል። |
ጳውሎስም እንደ ገና በወንድሞቹ ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀመጠ፤ በሰላምም ሸኙትና ወደ ሶርያ በባሕር ተጓዘ፤ ጵርስቅላና አቂላም አብረውት ነበሩ፤ ስእለትም ነበረበትና በክንክራኦስ ራሱን ተላጨ።
እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል።”
እርሱም፥ “ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር ናዝራዊ ነኝና ራሴን ምላጭ አልነካኝም፤ የራሴንም ጠጕር ብላጭ ኀይሌ ከእኔ ይነሣል፤ እደክማለሁም፤ እንደ ሌላም ሰው ሁሉ እሆናለሁ” ብሎ የልቡን ሁሉ ነገራት።
እርስዋም በጕልበቷ ላይ አስተኛችው፤ ጠጕር ቈራጭም ጠራች፤ እርሱም ሰባቱን የራሱን ጕንጕን ላጨው። ይደክምም ጀመረ፤ ኀይሉም ከእርሱ ሄደ።
እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።