“ስእለቱን የተሳለው የባለስእለቱ፥ እጁም ከሚያገኘው ሌላ ስለ ስእለቱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የቍርባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእለቱን እንደ ተሳለ እንደ ስእለቱ ሕግ እንዲሁ ያደርጋል።”
ዘኍል 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ከወይን የሆነውን ነገር ሁሉ ከውስጡ ፍሬ ጀምሮ እስከ ደረቀው ዘቢብ ድረስ አይብላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በናዝራዊነቱ ወቅት ከወይን ተክል የሚገኘውን ማንኛውም ነገር፣ የወይኑን ዘር፣ ግልፋፊውንም እንኳ ቢሆን አይብላ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ከወይን ጠጅ የሚሠራውን ሌላ ነገር ሁሉ እንዲሁም የውስጡን ፍሬ ወይም ግልፋፊውን እንኳ አይብላ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በናዝራዊነቱ ወቅት ከወይን ሐረግ የሚገኘውን ሁሉ የወይኑን ፍሬ ግልፋፊ ወይም ዘር አይብላ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ከወይን የሆነውን ነገር ሁሉ ከውስጡ ፍሬ ጀምሮ እስከ ገፈፎው ድረስ አይብላ። |
“ስእለቱን የተሳለው የባለስእለቱ፥ እጁም ከሚያገኘው ሌላ ስለ ስእለቱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የቍርባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእለቱን እንደ ተሳለ እንደ ስእለቱ ሕግ እንዲሁ ያደርጋል።”
ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን የተለየ ያድርግ፤ ከወይን ወይም ከሌላ ከሚያሰክር ነገር የሚገኘውን ሆምጣጤ አይጠጣ፤ የወይንም ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይንም እሸት ወይም ዘቢብ አይብላ።
“ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ ራሱን አይላጭ፤ ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ ቅዱስ ይሆናል፤ የራሱንም ጠጕር ያሳድጋል።
ከወይንም ከሚወጣው ሁሉ አትብላ፤ የወይን ጠጅንና የሚያሰክር መጠጥንም አትጠጣ፤ ርኩስንም ነገር ሁሉ አትብላ፤ ያዘዝኋትን ሁሉ ጠብቁ” አለው።