የምስክሩን ድንኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠራቸው።
ዘኍል 4:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምስክሩን ድንኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለማገልገል የሚመጡትን ከሠላሳ እስከ ዐምሳ ዓመት የሆናቸውን ወንዶች ሁሉ ቍጠር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቁጠራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ እስከ ኀምሳ ዓመት የሆናቸውን ወንዶች ሁሉ ቊጠር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመገናኛውን ድንኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠራቸው። |
የምስክሩን ድንኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠራቸው።
ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በምስክሩ ድንኳን ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡበትን ሁሉ ትለያለህ።
በምስክሩ ድንኳን ዘንድ ባለው አገልግሎታቸው ሁሉ፥ የድንኳኑ ሳንቆች፥ መወርወሪያዎቹም፥ ተራዳዎቹም፥ እግሮቹም፥ መሸፈኛዎቹም፥ መቀመጫዎቹም፥ የምስክሩ ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥
“የሌዋውያን ሕግ ይህ ነው፤ ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በምስክሩ ድንኳን ሥራ ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ።