በካህኑ በአሮን ልጅ በይታምር እጅ የሌዋውያን ተልእኮ ይሆን ዘንድ ሙሴ ከእግዚአብሔር እንደታዘዘ የምስክሩ ድንኳን ሥርዐት ይህ ነው።
ዘኍል 4:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌድሶን ልጆች አገልግሎት በምስክሩ ድንኳን ዘንድ ይህ ነው፤ ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከኢታምር እጅ በታች ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ የጌርሶናውያን ጐሣዎች በመገናኛው ድንኳን የሚኖራቸው አገልግሎት ይህ ነው፤ ተግባራቸውም በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አመራር ሥር ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌድሶናውያን ወገኖች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ይህ ነው፤ ሥራቸውንም የካህኑ የአሮን ልጅ ኢታማር ይቈጣጠራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የጌርሾን ልጆች አገልግሎት ይህ ነው፤ ሥራቸውንም የካህኑ የአሮን ልጅ ኢታማር ይቈጣጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጌድሶናውያን ወገኖች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ይህ ነው፤ ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከኢታምር እጅ በታች ይሆናሉ። |
በካህኑ በአሮን ልጅ በይታምር እጅ የሌዋውያን ተልእኮ ይሆን ዘንድ ሙሴ ከእግዚአብሔር እንደታዘዘ የምስክሩ ድንኳን ሥርዐት ይህ ነው።
የጌድሶን ልጆች አገልግሎት ሁሉ፥ በተራቸውም ሁሉ፥ በሥራቸውም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ ትእዛዝ ይሁን፤ በስማቸውና በተራቸውም ትቈጥራቸዋለህ።
በምስክሩ ድንኳን ዘንድ ባለው ሥራቸው ሁሉ የሜራሪ ልጆች ወገኖች አገልግሎት ይህ ነው፤ እነርሱም ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከኢታምር እጅ በታች ይሆናሉ።”