የቀረውም የመባ ወርቅ በእግዚአብሔር ፊት ይሠሩበት ዘንድ ንዋየ ቅድሳት ሆኖ ተሠራ። ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም ከቀይ ግምጃም ለመቅደሱ አገልግሎት ልብሶችን ሠሩ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለአሮን የተቀደሰውን ልብስ ሠሩ።
ዘኍል 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አመዱንም ያስወግዱ፤ መክደኛውንም በመሠዊያው ላይ ያድርጉ፤ ሐምራዊዉንም መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከናሱ መሠዊያ ላይ ዐመዱን ጠርገው ሐምራዊ ጨርቅ ያልብሱት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አመዱንም ከመሠዊያው ላይ ያስወግዱ፥ ሐምራዊውንም መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐመዱንም ከመሠዊያው ላይ ከጠረጉ በኋላ መሠዊያውን በሐምራዊ ጨርቅ ይሸፍኑት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አመዱንም ከመሠዊያው ላይ ያስወግዱ፥ ሐምራዊውንም መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ |
የቀረውም የመባ ወርቅ በእግዚአብሔር ፊት ይሠሩበት ዘንድ ንዋየ ቅድሳት ሆኖ ተሠራ። ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም ከቀይ ግምጃም ለመቅደሱ አገልግሎት ልብሶችን ሠሩ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለአሮን የተቀደሰውን ልብስ ሠሩ።
በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነትም ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች አመጡ።
የሚያገለግሉበትን ዕቃውን ሁሉ፥ ማንደጃዎቹን፥ ሜንጦዎቹንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ መክደኛዎቹንም፥ ያመድ ማፍሰሻዎቹን፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም የአቆስጣን ቍርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፤ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። ሐምራዊዉንም መጐናጸፊያ ወስደው ማስታጠቢያውንና ማስቀመጫውን ይሸፍኑት፤ በአቆስጣው ቍርበት መሸፈኛ ውስጥም አድርገው በመሸከሚያዎቹ ላይ ያኑሩት፤