እኛ ግን ለጦርነት ታጥቀን ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ በእስራኤል ልጆች ፊት እንሄዳለን፤ በዚህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆቻችን በተመሸጉ ከተሞች ይቀመጣሉ።
ዘኍል 32:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም፥ “የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች ሁላቸው የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ከእናንተ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ለጦርነት ዮርዳኖስን ቢሻገሩ፥ ምድሪቱንም ድል ብትነሡ ፥ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጡአቸዋላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አላቸው፤ “የጋድና የሮቤል ወንድ ሁሉ፣ እያንዳንዱ ለጦርነት በመዘጋጀት በእግዚአብሔር ፊት ከእናንተ ጋራ ዮርዳኖስን የሚሻገር ከሆነ፣ ምድሪቱም በእጃችሁ ስትገባ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ስጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ለጦርነት የተዘገጋጁት የጋድና የሮቤል ልጆች ሁሉ ከእናንተ ጋር በጌታ ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገሩ፥ ምድሪቱንም ድል ብትነሡ፥ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጡአቸዋላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የጋድና የሮቤል ሰዎች ዮርዳኖስን ተሻግረው በእግዚአብሔር መሪነት ለጦርነት የሚዘጋጁ ከሆነና በእነርሱም ርዳታ ምድሪቱን የምትወርሱ ከሆነ የገለዓድን ምድር ለእነርሱ ርስት አድርጋችሁ ስጡአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም፦ የጋድና የሮቤል ልጆች ሁላቸው ጋሻ ጦራቸውን ይዘው ከእናንተ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገሩ፥ ምድሪቱንም ድል ብትነሡ፥ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጡአቸዋላችሁ። |
እኛ ግን ለጦርነት ታጥቀን ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ በእስራኤል ልጆች ፊት እንሄዳለን፤ በዚህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆቻችን በተመሸጉ ከተሞች ይቀመጣሉ።
የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ከእናንተ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ወደ ጦርነት ባይሻገሩ ግን ልጆቻቸውን፥ ሚስቶቻቸውን፥ ከብቶቻቸውንም በፊታችሁ ወደ ከነዓን ምድር ንዱአቸው፤ በከነዓን ምድር በእናንተ መካከል ርስታቸውን ይወርሳሉ” አላቸው።
የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ገደሉአቸው፤ የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች፥ ለጋድም ልጆች፥ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።
ገለዓድንም፥ የጌሴሪያውያንንና የመከጢያውያንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳንንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥
ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመካከላቸው ለሌዋውያን ርስት አልሰጣቸውም።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ክህነት ርስታቸው ነውና ለሌዊ ልጆች በመካከላችሁ እድል ፋንታ የላቸውም፤ ጋድም፥ ሮቤልም፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀብለዋል።”
የሮቤልም ልጆች የጋድም ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ሄዱ፤ በሙሴም እጅ በተሰጠ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተቀበሉት ወደ ርስታቸው ወደ ገለዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ በከነዓን ምድር ካለችው ከሴሎ ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ተመለሱ።
ሳኦልም ዳዊትን፥ “ታላቂቱ ልጄ ሜሮብ እነኋት፤ እርስዋን እድርልሃለሁ፤ ብቻ ጀግና ልጅ ሁንልኝ፤ ስለ እግዚአብሔርም ጦርነት ተጋደል” አለው። ሳኦልም፥ “የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእርሱ ላይ አትሁን” ይል ነበር።