የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆችም ሙሴን እንዲህ ብለው ተናገሩት፥ “እኛ አገልጋዮችህ ጌታችን እንዳዘዘ እናደርጋለን።
ዘኍል 32:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቻችን ሚስቶቻችንም፥ እንሰሶቻችንም ሁሉ በዚያ በገለዓድ ከተሞች ይሆናሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቻችንና ሚስቶቻችን፣ የበግና የፍየል እንዲሁም የከብት መንጎቻችን እዚሁ በገለዓድ ከተሞች ይቀራሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቻችን፥ ሚስቶቻችንም፥ መንጎቻችንም፥ እንስሶቻችንም ሁሉ በዚያ በገለዓድ ከተሞች ይሆናሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስቶቻችንና ልጆቻችን፥ ከብቶቻችንና በጎቻችን፥ በዚህ በገለዓድ ከተሞች ይቈያሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቻችን፥ ሚስቶቻችንም፥ መንጎቻችንም፥ እንስሶቻችንም ሁሉ በዚያ በገለዓድ ከተሞች ይሆናሉ፤ |
የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆችም ሙሴን እንዲህ ብለው ተናገሩት፥ “እኛ አገልጋዮችህ ጌታችን እንዳዘዘ እናደርጋለን።
ነገር ግን እጅግ ከብቶች እንዳሉአችሁ አውቃለሁና ሴቶቻችሁና ልጆቻችሁ፥ ከብቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ከተሞች ይቀመጣሉ፤
ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ ከብቶቻችሁም ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ በዚች ምድር ይቀመጡ፤ እናንተ፥ ጽኑዓን ሁሉ ግን ታጥቃችሁ በወንድሞቻችሁ ፊት ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ ለእነርሱም ተዋጉላቸው።
የሮቤልም ልጆች የጋድም ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ሄዱ፤ በሙሴም እጅ በተሰጠ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተቀበሉት ወደ ርስታቸው ወደ ገለዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ በከነዓን ምድር ካለችው ከሴሎ ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ተመለሱ።