ዘኍል 32:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆችም ሙሴን እንዲህ ብለው ተናገሩት፥ “እኛ አገልጋዮችህ ጌታችን እንዳዘዘ እናደርጋለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጋድና የሮቤል ሰዎች ሙሴን እንዲህ አሉት፤ “እኛ አገልጋዮችህ ጌታችን ያዘዘንን እንፈጽማለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጋድና የሮቤልም ልጆች ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ጌታችን እንዳዘዘ እናደርጋለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጋድና የሮቤል ወገኖች እንዲህ አሉ፤ “እኛ አገልጋዮችህ፥ አንተ ጌታችን እንዳዘዝከው እናደርጋለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጋድና የሮቤልም ልጆች ሙሴን እንዲህ ብለው ተናገሩት፦ እኛ ባሪያዎችህ ጌታችን እንዳዘዘ እናደርጋለን። |
እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፥ “ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ እንሄዳለን።