ዘኍል 32:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ጠላቱ ከፊቱ እስኪጠፋ ድረስ ከእናንተ እያንዳንዱ ሰው የጦር መሣሪያውን ይዞ በእግዚአብሔር ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ጠላቶቹን ከፊቱ አሳድዶ እስኪያስወጣ ድረስ ሁላችሁም በእግዚአብሔር ፊት ለጦርነት ዝግጁ ሆናችሁ ዮርዳኖስን ብትሻገሩ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያሳድድ ድረስ ከእናንተ ለጦርነት የተዘጋጀው ሰው ሁሉ በጌታ ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጦር ሰዎቻችሁ ሁሉ ዮርዳኖስን መሻገር፥ በእግዚአብሔር አዛዥነት በጠላቶቻችን ላይ መዝመት፥ እግዚአብሔር ድል አድርጎ፥ ምድራቸውን እስኪወስድ ድረስ መዋጋት አለባቸው፤ ይህን ካደረጋችሁ በኋላ መመለስ ትችላላችሁ፤ በዚያን ጊዜ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለወገኖቻችሁ ለእስራኤላውያን ያለባችሁን ግዴታ ትወጣላችሁ፤ ከዚያ በኋላ ይህ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለው ምድር የእናንተ ርስት መሆኑን እግዚአብሔር ያረጋግጥላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያሳድድ ድረስ ምድሪቱም በእግዚአብሔር ፊት ድል እስክትሆን ድረስ ከእናንተ ሰው ሁሉ ጋሻ ጦሩን ይዞ በእግዚአብሔር ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገር፥ |
ምድሪቱም በእግዚአብሔር ፊት ድል እስክትሆን ድረስ ከዚያም በኋላ ትመለሳላችሁ፤ በእግዚአብሔርም ፊት በእስራኤል ዘንድ ንጹሓን ትሆናላችሁ፤ ይህች ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ርስት ትሆናችኋለች።
“የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዲህ ብሎ ያዘዛችሁን ቃል አስቡ፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር ያሳርፋችኋል፤ ይህችንም ምድር ይሰጣችኋል።