ዘኍል 23:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላቅም፥ “በዚያ እነርሱን ወደማታይበት ወደ ሌላ ቦታ እባክህ፥ ከእኔ ጋር ና፤ ከእነርሱ አንዱን ወገን ብቻ ታያለህ፤ ሁሉን ግን አታይም፤ በዚያም እነርሱን ርገምልኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ባላቅ፣ “እነርሱን ማየት ወደምትችልበት ወደ ሌላ ቦታ እንሂድ፤ በእዚያም ሁሉን ሳይሆን በከፊል ብቻ ታያቸዋለህ፤ እዚያም ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባላቅም እንዲህ አለው፦ “በዚያ ሆነህ እንድታያቸው፥ እባክህ፥ ከእኔ ጋር ወደ ሌላ ቦታ ና፤ ዳርቻቸውንም ብቻ ታያለህ፥ ሁሉን ግን አታይም፤ በዚያም ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባላቅም በለዓምን “ከእስራኤላውያን ሁሉን ሳይሆን ጥቂቱን ብቻ ወደምታይበት ወደ ሌላ ቦታ ከእኔ ጋር እንሂድ፤ በዚያ ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅም፦ በዚያ ሆነህ ታያቸው ዘንድ፥ እባክህ፥ ከእኔ ጋር ወደ ሌላ ቦታ ና፤ ዳርቻቸውንም ብቻ ታያለህ፥ ሁሉን ግን አታይም፤ በዚያም ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ አለው። |
ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።
እነሆም፥ የምድሩን ሁሉ ፊት ሸፈነ፤ በአቅራቢያችንም ተቀምጦአል፤ አሁንም ይህ ሕዝብ ከእኔ ይበልጣልና ልወጋቸውና ከምድሪቱ ላሳድዳቸው እችል እንደ ሆነ፥ ና ርገምልኝ፤ አንተ የመረቅኸው ምሩቅ፥ የረገምኸውም ርጉም እንደ ሆነ አውቃለሁና” ብሎ ይጠሩት ዘንድ መልእክተኞችን ላከ።
በሜዳ ወደ ተገነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰደው፤ አዞረውም፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፤ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን፥ አንድም አውራ በግ አሳረገ።
የሞዓብም ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ ተነሥቶ ከእስራኤል ጋር ተዋጋ፤ እንዲረግማችሁም የቢዖርን ልጅ በለዓምን ልኮ አስጠራው።