ዘኍል 2:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በመስዕ በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የዳንም ልጆች አለቃ የአሚሳዲ ልጅ አክያዜር ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰሜን በኩል፤ የዳን ምድብ ሰራዊት በዐርማው ሥር ይሆናል፤ የዳን ሕዝብ አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ሲሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በሰሜን በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የዳንም ልጆች አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስተ ሰሜን በኩል በዳን ክፍል ዓርማ ሥር የሚሰፍሩ ወገኖች ናቸው፤ የዳን ነገድ መሪ የዓሚሻዳይ ልጅ አሒዔዜር ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰሜን በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የዳንም ልጆች አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበረ። |
የዳን ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደእየ ስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥
ከሠራዊቱ ሁሉ በኋላ የዳን ልጆች ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊታቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚሳዲ ልጅ አኪያዜር አለቃ ነበረ።
ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት ጊደሮች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ የአሚሳዲ ልጅ የአኪያዜር መባ ይህ ነበረ።