ዘኍል 2:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከዚያም በኋላ የምስክሩ ድንኳን፥ በሰፈሮቹም መካከል የሌዋውያን ወገን ይጓዛል፤ እንደ አሰፋፈራቸው ሰው ሁሉ በየስፍራው፥ በየዓላማውም ይጓዛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ የመገናኛው ድንኳንና የሌዋውያን ምድብ በመካከል ሆነው ይጓዛሉ፤ እያንዳንዳቸውም አሰፋፈራቸውን በመከተል ቦታቸውን ጠብቀው በዐርማቸው ሥር ይጓዛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከዚያም በኋላ በሰፈሮቹም መካከል የመገናኛው ድንኳን ከሌዋውያን ሰፈር ጋር ይጓዛል፤ እንደ ሰፈራቸው እያንዳንዱ ሰው ስፍራቸውን ይዘው በየዓላሞቻቸው ይጓዛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያዎቹ ሁለት ክፍሎችና በመጨረሻዎቹ ሁለት ክፍሎች መካከል ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን ይዘው ይጓዛሉ፤ እያንዳንዱም ክፍል ሰፈሩ ተለይቶ በሚታወቅበት ዓርማ ሥር ምድብ ተራውን ጠብቆ ይጓዛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በኋላ የመገናኛው ድንኳን በሰፈሮቹም መካከል የሌዋውያን ሰፈር ይጓዛል፤ እንደ ሰፈራቸው ሰው ሁሉ በየስፍራው በየዓላማውም ይጓዛሉ። |
“በባሕር በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የኤፍሬም ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የኤሜሁድ ልጅ ኤሌሳማ ነበረ።
በምሥራቅ በኩል በምስክሩ ድንኳን ፊት የሚሰፍሩት ሙሴና አሮን ልጆቹም ይሆናሉ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ሕግም የመቅደሱን ሕግ ይጠብቃሉ፥ ከሌላ ወገን የዳሰሰ ቢኖር ይገደል።
እኔ በሥጋ ከእናንተ ዘንድ ባልኖርም እንኳን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ እነሆ ጠባያችሁንና ሥርዐታችሁን፥ በክርስቶስም ያለ የእምነታችሁን ጽናት ስለ አየሁ ደስ ይለኛል።