የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ ከኤልያብ ልጆች ከዳታንና ከአቤሮን፥ ከሮቤልም ልጅ ከፋሌት ልጅ ከአውናን ጋር ተናገረ።
ዘኍል 16:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለማኅበሩ፦ ከቆሬ ማኅበር ዙሪያ ፈቀቅ በሉ ብለህ ንገራቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ማኅበሩን ‘ከቆሬ፣ ከዳታንና ከአቤሮን ድንኳኖች ራቁ’ በላቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለማኅበሩ እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ከቆሬና ከዳታን ከአቤሮንም ማደሪያ ዙሪያ ርቃችሁ ገለል በሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለማኅበሩ፦ ከቆሬና ከዳታን ከአቤሮንም ማደሪያ ዙሪያ ፈቀቅ በሉ ብለህ ንገራቸው። |
የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ ከኤልያብ ልጆች ከዳታንና ከአቤሮን፥ ከሮቤልም ልጅ ከፋሌት ልጅ ከአውናን ጋር ተናገረ።