በነጋውም ዳዊት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሠዋ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ አንድ ሺህ ወይፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦቶች፥ የመጠጥ ቍርባናቸውንም፥ ስለ እስራኤልም ሁሉ ብዙ መሥዋዕት አቀረበ።
ዘኍል 15:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመጠጥ ቍርባንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን የኢን መስፈሪያ ሦስተኛ እጅ ወይን ታቀርባለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን የሂን አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ አዘጋጁ፤ ይህንም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሽታ ያለው አድርጋችሁ አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን የኢን መስፈሪያ ሢሶ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን ታቀርባለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመጠጥ ቊርባን የሊትር አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ፤ ይህም ሁሉ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል፤ |
በነጋውም ዳዊት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሠዋ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ አንድ ሺህ ወይፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦቶች፥ የመጠጥ ቍርባናቸውንም፥ ስለ እስራኤልም ሁሉ ብዙ መሥዋዕት አቀረበ።
ከአንዱ ጠቦትም ጋር የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመጠጥ ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ።
ለአንዱም አውራ በግ የሚቃጠል ቍርባን ወይም መሥዋዕት ባደረጋችሁ ጊዜ የኢን መስፈሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቍርባን ታዘጋጃላችሁ።
ለሚቃጠልም መሥዋዕት፥ ወይም ለሌላ መሥዋዕት፥ ወይም ስእለትን ለመፈጸም፥ ወይም ለደኅንነት መሥዋዕት ከላም ወገን ለእግዚአብሔር ብታዘጋጅ፥
“የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ ቍርባኔን፥ መባዬንና የበጎ መዓዛ መሥዋዕቴን በበዓላት ቀኖች ታቀርቡልኝ ዘንድ ጠብቁ።
የመጠጡም ቍርባን ለአንድ ጠቦት የኢን መስፈሪያ አራተኛው እጅ ነው፤ በመቅደሱ ውስጥ ለእግዚአብሔር ለመጠጥ ቍርባን መጠጥ ታፈስሳላችሁ።
አንድ ሌማትም በዘይት የተለወሰ የስንዴ ቂጣ እንጀራ፥ በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ የእህሉንም ቍርባን፥ የመጠጡንም ቍርባን ያቅርብ።
ወይኑም፦ እግዚአብሔርንና ሰውን ደስ የሚያሰኘውን የወይን ጠጅነቴን ትቼ በዛፎች ላይ እነግሥ ዘንድ ልሂድን? አላቸው።