ዘኍል 15:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአንዱም አውራ በግ የሚቃጠል ቍርባን ወይም መሥዋዕት ባደረጋችሁ ጊዜ የኢን መስፈሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቍርባን ታዘጋጃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከአውራ በግ ጋራ በሂን ሢሶ ዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አዘጋጁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአንዱም አውራ በግ የኢን መስፈሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ መልካም ዱቄት ለእህል ቁርባን እንዲሆን ታዘጋጃለህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አውራ በግ መሥዋዕት ሆኖ በሚቀርብበት ጊዜ ደግሞ በአንድ ሊትር ተኩል የወይራ ዘይት የተለወሰ ሁለት ኪሎ ዱቄት አቅርቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአንዱም አውራ በግ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የኢን መስፈሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቍርባን ታዘጋጃለህ፤ የኢን መስፈሪያ ሢሶም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን ታቀርባለህ። |
ቍርባኑን ለእግዚአብሔር የሚያቀርብ የኢፍ መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ እጅ የሆነ የመልካም ዱቄት መሥዋዕት ያመጣል።
ለመጠጥ ቍርባንም የኢን መስፈሪያ የሆነ መልካም ዱቄት አራተኛ እጅ በሚቃጠለው መሥዋዕት ወይም በእህሉ ቍርባን ላይ ያደርጋል፤ ለእያንዳንዱ ጠቦት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥዋዕት ይሆን ዘንድ ይህን ያህል ያድርግ።