በሕዝቡ ላይ ሁል ጊዜ ይፍረዱ፤ የከበዳቸውን ነገር ወደ አንተ ያምጡት፤ ቀላሉን ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ ያቃልሉልሃል፤ ይረዱሃልም።
ዘኍል 15:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰንበት ቀን ዕንጨት ሲለቅም ያገኙትም ሰዎች ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ አመጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕንጨት ሲለቅም ያገኙትም ሰዎች ሰውየውን ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው የእስራኤል ማኅበር አመጡት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንጨትም ሲለቅም ያገኙት ሰዎች ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ ማኅበሩም ሁሉ አመጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያዙትም ሰዎች መላው ማኅበር ወዳለበት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወሰዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንጨትም ሲለቅም ያገኙት ሰዎች ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ ማኅበሩም ሁሉ አመጡት። |
በሕዝቡ ላይ ሁል ጊዜ ይፍረዱ፤ የከበዳቸውን ነገር ወደ አንተ ያምጡት፤ ቀላሉን ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ ያቃልሉልሃል፤ ይረዱሃልም።