ሙሴም፥ “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረፍት፥ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ ነገ የምትጋግሩትን ዛሬ ጋግሩ፤ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፤ የተረፈውንም ሁሉ ለነገ እንዲጠበቅ አኑሩ” አላቸው።
ዘኍል 15:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች በምድረ በዳ ነበሩ፤ አንድ ሰውም በሰንበት ቀን ዕንጨት ሲለቅም አገኙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ አንድ ሰው በሰንበት ቀን ዕንጨት ሲለቅም ተገኘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች በምድረ በዳ ሳሉ አንድ ሰው በሰንበት ቀን እንጨት ሲለቅም አገኙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በምድረ በዳ ሳሉ አንድ ጊዜ አንድ ሰው በሰንበት ቀን የማገዶ እንጨት ሲለቅም ተያዘ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች በምድረ በዳ ሳሉ አንድ ሰው በሰንበት ቀን እንጨት ሲለቅም አገኙ። |
ሙሴም፥ “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረፍት፥ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ ነገ የምትጋግሩትን ዛሬ ጋግሩ፤ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፤ የተረፈውንም ሁሉ ለነገ እንዲጠበቅ አኑሩ” አላቸው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ራሳችሁን ጠብቁ፥ በሰንበትም ቀን ምንም ሸክም አትሸከሙ፤ በኢየሩሳሌምም በሮች አታግቡ፤